Patriotic Dereje, we have the Highest Honor the sacrifys You paid for the Amara Well-bieng Freedom!!!

Our Heroes

የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ የሕይወት ዘመን ታጋይ የአማራ ፋኖ ራስ በሚል ለአርበኛ ደረጀ በላይ ካወጣው የክብር መግለጫ ላይ የተወሰደ

"…ጎንደር ደምቢያ ምድር ያለእረፍት ውጊያ የቀጠለው በዕዛችን የዘመቻ መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ደረጀ በላይ ቆራጥ አመራር፤ በትግል ወንድሞች የውጊያ ቅንጅት፤ በሕዝባችን ጥንካሬ ነው!!

ከአዕምሮ በላይ የጀብድና የውጊያ ጥበብ ባለቤት የሆነውአርበኛችን ለከፈልክልንና እየከፈልክልን ላለው ውድ ዋጋባለዕዳዎችህ ነን። ታሪክ አዋቂው አማራ ሁሉንም እየመዘገበነው።

ከራስ በላይ የሕይወት ዘመን ታጋይ አርበኛ ደረጀ በላይ፡-

መሪ ነው፡- ከነመላ ቤተሰቡ ለአማራ ሕዝብ ነጻነት ትግል ሜዳ ቀድሞ የወረደ፡፡ ባለ ራዕይ ነው ሩቅ ዓላሚ፡፡ ቆራጥ ነው፤ የውሳኔ ባለቤት፡፡ ከግለሰብ ሩጫ ይልቅ ለተቋማዊ ትግልየታመነ፤ ለጋራ ድል የቆመ፤ ለሕዝብ ነጻነት የመነነ የትግል መሪያችን ነው!!

አባት ነው፡- ጀግኖችን የወለደ፤ ጀግኖችን ያሳዳገ፤ በትግል ሜዳ ጀግና ፈጣሪ፤ ጀግና አክባሪ ነው፡፡ ሰራዊቱን በትህትና፣ ትግሉን በጥበብ የሚመራ፤ በዕዝ፣ በክፍለ ጦሮች፣ በየ አሀዱ ቅራኔዎች ሳይውሉ ሳያድሩ በትኩሱ የሚሽር፣ አስታራቂ ዳኛ የትግሉ አባትነው!!

ለጋስ ነው፡- ለአማራ ሕዝብ ሕልውና ትግል ቤት ንብረቱንያጣ፤ ትላንት በገንዘቡ ገዝቶ ያስታጠቀ፣ ዛሬ ማርኮ ሸላሚ ነው! በትግሉ አባ ናደውን አምኖ የተከተለ ወጣት ሁሉ ታጥቋል፤ትጥቁ የብረት ብቻ ሳይሆን የአማራነት ጭምር ነው። አማራዊ የውጊያ ሥነ-ልቦና ከብረት ጋር የሚያስታጥቅ፤ ደሙንም ሀብቱምን የሚሰጥ ለጋስ ነው!!

አዋጊ ነው፡- በውስን የሰው ኃይል የመሬት እርባና (ገጽታ) ተጠቅሞ ጠላትን የእንብርክክ የሚነዳ፤ በምርኮ ናዳ ወገንን በድል ቁንጣን የሚያጨናንቅ! ለጠላት እሳት፤ ለወዳጅ ድል አጉራሽ ነው፡፡

ዘመቻ ማቀድ፣ መከወን፣ መገምገም፣ ማረም፣… መክሊቱ የሆነለት የድል መሪያችን አባ ናደው ለከተማ ውጊያ ‹ሰርጂካል ኦፕሬሽን› የውጊያ ዕቅድ በማውጣት የሚመራ፣ የዐቢይአሕመድ የግል ጀኔራሎችን እንቅልፍ የነሳ፣ የብልፅግናን አራዊት ሰራዊት አሰልፎ የነዳ የውጊያ ፈላስፋ ነው።

ይህ የሕይወት ዘመን ታጋይ መሪ አርበኛችን የፋኖ ራስ፡- ሙስሊም ክርስቲያን አክባሪ የትግልም የሞራልም አባት ነው፡፡ ለከፈለው ዋጋ ካህን ሼኹ የሚፀልይለት፣ እናቶች የሚሳሱለት፣አባቶች በምክር ያልተለዩት፣ ወጣቶች የሚከተሉት፣ እረኞችየሚቀኙለት፣ … ከራስ በላይ ለሕዝብ የኖረ የሕይወት ዘመንታጋይ ነው፡፡

የአማራ ፋኖ ራስ፣ አርበኛ ደረጀ በላይ እኛ አማራዎችለከፈልክልን ውድ ዋጋ ሁሉ ከፍለነው የማንዘልቀውባለዕዳዎችህ ነን። አንተ የአማራ ትግል ቀንዲል፤ የአማራ የብረት አጥር፤ የዕዛችን ኩራት ነህ፤ መሪያችን ነህና እስከቀራኒዩ እንከተልሃለን!!

በሞት ሸለቆ ሳይታለፍ ታሪክ መቀየር እንደማይቻል ቤዛ ሆነው ያሳዩን ወንድሞቻችን ሁሌም በልባችን ይኖራሉ፡፡ የወንድሞቻችን መስዋዕትነት የአማራን የህልውና ትግል ለዘላቂ ድል ለማብቃት የአብዮቱን ባቡር ያፈጥነዋል እንጅ ከቶውንም አያዘገየውም፡፡ የታጋዮቻችን ሰማዕትነት በአማራ ፋኖ ዘንድ ከፍተኛ የትግል መነሳሳት፣ እልህና ቁጭት በመፍጠር የአገዛዙን ሥርዓተ ቀብር አይቀሬ ያደርገዋል፡፡

አርበኛ ደረጀ በላይ (አባ ናደው) ይህን ሁሉ ዋጋ የከፈልከውለአማራ ህልውና በመሆኑ በትውልዱ ልብ ውስጥ በታሪክስትዘከር ትኖራለህ!! በትግሉ ሜዳ የፀናህ ነህና ባንተ መሪነት በሚሊዮን ልጆችህ ታጋይነት የአማራ ሕዝብ ነጻነት ይረጋገጣል!!

እናመሰግናለን መሪያችን!! እናመሰግናለን ጀግኖቻችን!!

Previous
Previous

ቀራቅርና ሐሙሲት በፋኖ እጅ ዙ23 ተማርኳል

Next
Next

Eritrea Government Announces to Support Amhara’s Well-bieng strugle