የሜኔሶታ ኒያላ ~
ይህን ያውቁ ኖራል ?
በሰሜን አሜሪካ የኢትዮጵያ ስፖርት ፌዴሬሽን ውስጥ ከ1987 ጀምሮ የሚሳተፈው የሜኔሶታ ኒያላ ቡድን ለፌዴሬሽኑ ቀላል የማይባሉ አስተዋፆዎች ያደረገ አንጋፋ ክለብ ነው።
ፌዴሬሽኑ በተቋቋመ በ3ተኛው አመት የተቀላቀለው የኒያላ ቡድን ሁለት ጊዜ ለግማሽ ፍፃሜና ሁለት ጊዜ ደግሞ ለዋንጫ (1999 እና 2002) የደረሰ በሜዳ ላይ ልዩ ችሎታ ያሳየና የብዙዎችን ቀልብ የሳበ ክለብ ነው።
የሜኔሶታው ኒያላ ቡድን የቀድሞው የኢትዮጵያ መብራት ኃይል ብሄራዊ ቡድን ተጫዋች እንዲሁም በኢትዮጵያም በሜኒሶታም በአሜሪካ ለበርካታ አመታት አሰልጣኝ የነበረውና የፌዴሬሽኑ የቶርናመንት ክፍል ሃላፊ የነበረው ታዋቂው የእግር ኳስ ሰው ሪኮ ጂላርዲ ቤት ነው። ሪኮ ለኒያላ ቡድንም ለፌዴሬሽኑም በቦርድና ስራ አስፈጻሚነት ብዙ ግልጋሎት የሰጠ ሰው ነበር–ነፍስ ይማር!
በ1998 የኒያላ ቡድን የቀድሞው የመብራት ኃይልና የብሄራዊ ቡድን ተጫዋች የነበረው ጠንክር አስናቀ ቡድኑን ተቀላቀለ:: ጠንክር በ1993 በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር 24 ጎል በማግባት የኢትዮጵያ የአንደኛ ዲቪዢዮን የክለቦች ውድድር ያሸነፈና ኮከብ ግብ አግቢ ለመሆን የበቃ ድንቅ ተጫዋች ነበር:: ከ1994 ጀምሮ ለሎስ አንጀለስ ዳሎል ይጫወት ነበር:: ኑሮውን ወደ ሜኔሶታ ከቀየረና የጨዋታ ጊዜውን እስኪጨርስ ለኒያላ ተጫውቶ በፌዴሬሽኑ ታሪክ በጎል አግቢነቱ: ጥንካሬውና ፍጥነቱ እስካሁን ይወራለታል:: ከጠንክር ጋር ከተጫወቱና የሚታወስ ብቃታቸውን ያሳዩ ብዙ ድንቅ ተጫዋቾች ቢኖሩም ባቲ, ዮሴፍ እና ጌታቸው ግን የማይረሱ ናቸው::
በፌዴሬሽኑ ታሪክ አሻራቸው ከሚጠቀሱ የሜኒሶታ ኢትዮጵያውያን አንዱ ሰለሞን ሃይሌ ወይንም በብዙዎች የሚታወቀው Sol Design ነው:: ሶል ፌዴሬሽኑ አዲስ የሎጎ ለውጥ ባደረገበት በ2004 አሁን በስራ ላይ ያለውን የመጀመሪያ ሎጎ ያረቀቀ የማይረሳ ግለሰብ ነው::
ሜኒሶታ ከ1987 ጀምሮ የኒያላን ቡድን በፌዴሬሽኑ የቦርድ እና በስራ አስፈጻሚ አባልነት በነፃ በማገልገል ለድርጅቱ ትልቅ አስተዋጽኦ ያደረጉ ብዙ የምንኮራባቸው ኢትዮጵያንን አሉ:: ከእነዚህ ውስጥ አሁን በፌዴሬሽኑ ካሉት አቶ ንጋቱ መኩሪያ እና አስቤ ሃይሉ በተጨማሪ አቶ ተድላ: በላይነህ: እንዲሁም በቦርድም በአሰልጣኝነትም ዘውዱ አበበ: በቦርድና በስራ አስፈጻሚነት ያገለገለው አቶ ዘካርያስ ጌታቸው በዋናነት ይጠቀሳሉ::
ስማቸው ያልተጠቀሱ ተጫዋቾች: ቦርድ አባላት: የከተማው የክለብ ደጋፊዎች እንዲሁም ባለቤቶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው በሙሉ ላለፉት 40 አመታት ላበረከቱት አስተዋጽኦ ፌዴሬሽኑ ልባዊ ምስጋናውን ያስተላልፋል!
በሜኔሶታ እንኮራለን። እንኳን ለ43ኛው አመታችሁ አደረሳችሁ!
ዘንድሮ ደሞ 43ተኛው የፌዴሬሽኑን ዝግጅት ታሪካዊ ለማድረግ ክለቡም የከተማው አዘጋጅ ኮሚቴ በከፍተኛ ዝግጅት ላይ ነው። ማህበረሰቡ የንግድ ተቋማቱ ይህን ዝግጅት ቀለማዊ ለማድረግ በተጠንቀቅ ላይ ናቸው።
ሜኔሶታ የ10″000 የሐይቆች ባለቤት, የግዝፉ በአሜሪካ ቁጥር አንድ የMall of America ባለቤትና ለጉብኝት የተመረጠ State ነው።
30 ቀን የቀረው !
ሜኔሶታ አይቀርም
ኢትዮጵያዊነት ኩራት ነው !
Did you know this?
Since 1987, the Minnesota Nyala team has been participating in the Ethiopian Sports Federation in North America and is one of the federation’s long-standing clubs that has made significant contributions. Joining the federation in its third year, the Nyala team reached the semifinals twice and the championship finals twice (in 1999 and 2002). The club demonstrated exceptional talent on the field and captured the hearts of many fans.