የጎንደር ልሂቃን ጤናማ ጎንደሬነትን እውን ማድረግ ይጠበቅብናል!!!
—————————-//////————————–
እንደሚታወቀው ጎንደሬነት ማንነት አይደለም!!!
ጎንደሬነት ከጋይንት እስከ ወልቃይት የተዘረጋውን በታሪክ፣በቱሪዝም፣በባህል፣በምርጥ የህዝብ እሴቶች ፣በእምቅ የተፈጥሮ ሃብት ፣ በጀግንነት፣በእንግዳ ተቀባይነት እና ሃይማኖተኛነት የደመቀው ጎንደር የሚባለው ሰፊ ታሪካዊ ምድር ስነ-ልቦናዊ ገጽታው የሚገለጽበት ዐውድ ነው!!!
በ17ኛው ክ/ዘመን በዓለም ሰማይ ጠቀስ የሚባል ስልጣኔ ከነበራቸው የአለም አካባቢዎች አንዱ የሆነው ጎንደር ከጎረቤታችን አካባቢ በእንግድነት መጥቶ እና በእምነት ወደ ነጋሲያኑ የመጠጋት ዕድል አግንቶ የነበረው ራስ ሰዑል ሚካኤል የመጨረሻውን የጎንደሬዎቹ ዘመን ንጉሰ-ነገስት አጼ ተ/ጊዮርጊስ በጨርቅ አንቆ ከገደለ በሗላ የጎንደር ከፍታ እንዲያከትምና ዘመነ -መሳፍንት (Era of Princes) የተሰኘው የጨለማ ዘመን እውን እስኪሆን ድረስ ጎንደር ከ253 ዓመታት በላይ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ ሆናም አገልግላለች!!!
ሆኖም ጎንደርን ወደ ቀደመ ገናና ከፍታዋ ለመውሰድ ጤናማ ጎንደሬነት እውን መሆን ይኖርበታል!!!
ጤናማ ጎንደሬነት ሲባል እንደኢትዮጵያ ወደፊት አገራዊ የልሂቃን መግባባት (National Elite Consensus) በሚደረስበት አገራዊ የአስተዳደር ዘይቤ መሠረት የላቀ ሚና በመጫወት :-
1/ አሁን ያለው የብሔር ፌዴራሊዝም የአስተዳደር ዘይቤ የሚቀጥል ከሆነ ጎንደሬው ከሌሎች የአማራ እህት ወንድሞቹ ጋር ባሉ ችግሮች ዙሪያ እውነተኛ ውይይት በማድረግ በወርዱ እና ቁመቱ ልክ ውክልና እና የልማት ድርሻ እንዲኖረው አድርጎ እና ያሉ የፍትሐዊነት ችግሮችን አርሞ በአማራነት የትብብር ማዕቀፍ በመቀጠል የጎንደርን ከፍታ እውን ማድረግ
2/የብሔር ፌዴራሊዝም በኢትዮጵያ የሚቀር እና ጂኦግራፊያዊ የአስተዳደር ዘይቤ የሚመጣ ከሆነ ደግሞ ሙሉ የትብብር አቅምን አሟጦ ተጠቅሞ የጎንደርን ከፍታ እውን ማድረግ
3/ ጎንደር ውስጡ ላይ ያሉ ችግሮችን ደግሞ ለሌሎች መጠቀሚያ ሳይሆን በሩን ዘግቶ በመምከር ከፍታውን የሚመጥን አንድነትን እውን ማድረግ!!!
#መውጫ:-ከላይ ከተገለጹት አግባቦች ውጭ ከሌላው አካባቢ ራስን ነጥሎ ጎንደርን ክልል እናድርግ ከሚሉ እና ሌሎች የጥላቻ እሳቤዎች ከሚስተናገድባቸው የወደቁ አመላካከቶች ራስን ነጻ ማድረግ ያስፈልጋል !!!
ቀኝም ነፈሰ ግራ የሁሉም ሰው ትኩረት መሆን ያለበት ግን ጎንደር የሚገባትን ልማት እና ክብር በወርዷ እና ቁመቷ ልክ ማግኘት አለባት!!!
May be an image of ‎horizon and ‎text that says '‎5:44 ما ف A G 60% ሞህ‎'‎‎

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top