ህያው ጀግና ቀኝ አዝማች ጨለፍ ተስፋው ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም ውድ ህይወቱን ለአማራ ህዝብ ህልው መሆን አሳልፎ ሰጠ! አርበኛ ጨለፍ ተስፋው የአባቱን ክላሽ በማንሳት በ2013 ዓ.ም ጋሸና ግባር ላይ ተከሰተ!

 

No photo description available.

By
Arbegna Abebe Fentaw
ህያው ጀግና ቀኝ አዝማች ጨለፍ ተስፋው ሚያዚያ 21/2018 ዓ.ም ውድ ህይወቱን ለአማራ ህዝብ ህልው መሆን አሳልፎ ሰጠ!
አርበኛ ጨለፍ ተስፋው የአባቱን ክላሽ በማንሳት በ2013 ዓ.ም ጋሸና ግባር ላይ ተከሰተ። ብላቴናው በሰሜኑ ጠርነት እልክ አስጨራሽ ተጋድሎ በማድረግ በድል ተራራ ላይ ታሪኩን በደም ፃፈ። የሰሜኑ ጦርነት አደቡን እንደያዘ አርበኛ ጨለፍ ተስፋው በአምባሰል ተራሮች እየተጎባለለ ከስምንት ጓዶቹ ጋር ፋኖን ማሰባሰብ ጀመረ። ሰማዕቱ ራምቦ የጨለፍ የአንጀት ወዳጅ ከመሆኑ የተነሳ ሁለታቸው አብረው ለበርካታ አመታቶች የጥላትን ሰራዊት በደፈጣ ዶግ አመድ እያደረጉ ዘመን ተሻጋሪ ወደር አልባ ታሪክን በፋኖነት ስም አስመዘገቡ። አርበኛ እራቦና ጨለፍ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች ናቸው። አርበኛ ጨለፍ ከአምባሰል ተራሮች ተነስቶ ሸዋ ምድር ተከስቶ በርካታ ታሪኮችን ከሰራ በኋላ ወደ ምዕራብ ወሎ ተቀሳቅሶ በወግዴ፤በሳይንትና በሌሎች ወረዳዎች ፋኖን በማደራጀት ጉልህ ሚናን ተጫውቷል።
አሞካሽተው ቀኜ ብለው የሚጠሩት ቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው ከሸዋ ምድር አንድ ታላቅ ታሪክን ለመስራት በደራ በኩል ተከሰተ። እርሱ የሚገድበው ቀጠና የለምና በአገዛዙ በአብይ አህመድ ተሰርተው ሰልጥነውና አቅጣጫ ተሰቷቸው በጃልሰኒ የሚመሩ አካላቶች በአማራ ህዝብ ላይ አሰቃቂ ግፍን ይፈፅሙ ነበርና፤ ቀኝአዝማች ጨለፍ በደራ በኩል ጃልሰኒና ቡድኖቹ ወደሚገኙበት አቀና። ያኔ ጃልሰኒ የአማራን ንፁሀኖችን መጨፍጨፍ የዘወትር የአብይዚም ተልኮው ስለነበር የጨለፍን ነፍጥ ፈፅሞ አልጠበቀም። ጨለፍ ግን የአማራን ህዝብ የጨፈጨፈን ጥላት ከከተመበት ድረስ ዘልቆ የህልውና መዳኛ ነፍጡን በነ ጃልሰኒ አርከፈከፈው። በርካታ የጃል ሰኒ ሰራዊቶች ተደመሰሱ። ጃልሰኒም ወደ አለቃው አብይ አህመድ እሩጦ እጀን ሰጠሁ አለ። የእሳቱ ጉራጅ ጨለፍ ተስፋው በደራ ምድር በጀብደኝነት በአማራዊ ኩራት ጎልቶ ታዬ። አፀፋ ጥቃቱን በሚገባ የተወጣው አርበኛ የአብይ አህመድንና የሽመልስ አብደሳን ገዳይ መሪ ጃልሰኒን በማስጨነቅ የጥፋት ካባውን ገፈፈው።
ቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው የደራን ኦፕሬሽን በሙሉ ፈፅሞ ወደ ወግድ ተሻገረ። ወዳውኑ ወደ ትውልድ ቦታው መቄት በመሻገር ከጓድኛው አርበኛ ቅዱሴና አርበኛ ማረጉ እንድሁም በርካታ አርበኛ ወንድሞቹ ጋር በመሆን ታሪኩ ተነግሮለት የማያቀውን የመቄትን ህዝብ ታሪክ በደም በአጥንታቸው ለመፃፍ ቆርጠው ተነሱ። በመቄት ምድር ፋኖነትን ለማስፋፋት ከቀናቶች የዘለለ ጊዜ ሳይውስድባቸው ሳር ቅጠሉን በፋኖ አንቆጠቆጡት። በመቄት ምድር ላይ ጥላት የእግሩ መረገጫ እስኪያጣ ድረስ ቀኝ አዝማች ጨለፍ ተስፋው ቆላ ወርዶ ዳገት ተቃቶ ፋኖን አደራጀ። የፋኖ ትግልን ጠላፊዎች ጨለፍን ከአንድም ሁለት ሶስት ጊዜ በሴራ ትብታባቸው ሊታቱት ሞከሩ እንጅ ከአማራነት ክብሩ ፈፅሞ የሰናፍጭ ቅንጣት ያክል ሊያሳጡት አልተቻላቸውም። በርካታ ሆድ አደር የአማራ ህዝብ ጥላቶች ቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋውን እንደ ተኩላ ከበው ይጠዘጥዙት ዘንድ ቋመጡ።ቀኝአዝማች ጨለፍ ግን ወይ ሞት ወይ አማራነት በማለት እስከ ህይወት ፍፃሜው ድረስ በአማራዊያን የአባቶቻችን ታሪክ ቁሞ ተገኜ። በዚህ አቋሙ በርካታ ባንዳዎች የልመና በራፋቸውን ለማስከፈት በቀኝአዝማች ጨለፍ ላይ የሀሰት ትርክትና ስም ማጥፋት ዘመቻ ቢከፍቱበትም ቅሉ እስከ ሞት ድረስ በአላማው ፀንቶ ዘለቀ።
የደፈጣው ንጉስ ቀኝአዝማች ጨለፍ ተስፋው ለአማራ ህዝብ ታምኖ ከኦሮሙማው ጥላት ጋር ከሶስት አመት በላይ ሲፋለምና የጥላትን ሰራዊት በየቀኑ በአስከሬን አንስተህ ጫን በመቄት ወረዳ የምስጥ ሲሳይ እያደረገ በርካታ አካባቢዎችን ከጥላት ነፃ በማውጣት የፌደራል ጥቁር አስባልት መቆጣጠር ቻለ። ቀኝ አዝማች ጨለፍ መነሻ ቦታውን መቄት ያድርግ እንጅ በድርጅቱ የሚሰጠውን ግዳጅ ከቦታ ቦታ በመንቀሳቀስ በርካታ ታሪኩችን መስራት የቻለ የዘመናችን በላይ ዘለቀ ነበር። ቀኝአዝማች ጨለፍ ከሶስት ወራቶች በፊት በተንታ አጅባርና በተንታ ሚካኤል የቀድሞዉ የደጋው መብረቅ የአሁኑ 106ኛ ኮር ዘመቻ መሪ ሆኖ የጥላት ሙሉ ሰራዊትን ሙሉ በሙሉ በመደምሰስ ህያው ታሪክን ሰርቷል። በብዙ ፈተናዎች ውስጥ 106ኛ ኮርን ለመመስረት ጨለፍ እጅግ የላቀ ሚናን በማድረግ ኮሩ በሁለት እግሩ እንድቆም አይረሴ አስተዋፆ ነበረው። በቁልምጫ ቀኜ እያልን የምንጠራው ተናዳፍው አርበኛ ከወሎ እስከ ሸዋ ከሸዋ እስከ ጎንደር ጎጃም እግሮቹ እስኪቀጥኑ ተከራቶ አማራዊ ግዳጁን በመወጣት ተከድቶ እስኪወድቅ ድረስ በፍፁም ታማኝነት ተወጥቷል።
በደቡብ ጎንደር የቀድሞዋን አንሻ ክፍለ ጦር የአሁኗ 22ኛ ክፍለጦርን በመምራት ንፋስ መውጫ የጥላት ሀይልን በመደምሰስ እና በርካቶችን በመማረክ ቀጠናዊ ትስስርን በማይዝል ቃልኪዳን አስተሳስሯል። ቀኝአዝማች ጨለፍ በርካታ ክፍለ ጦሮች ላይ ትልቅ አስተዋፆ ከማድረጉም በላይ የአማራ ታጋዮች አንድ እውነተኛ ድርጅት እንድኖረው ጉልህ ሚናን ተወቷል።
በመጨረሻም አርበኛ ቀኝ አዝማች ጨለፍ አስፋው ባመነውና ጓዴ ባለው ጥቁር አማራ ከጀርባው ተወግቶ ወደቀ። ለአማራ ህዝብ ነፃነት ትክ አልባ ህይዎቱን ሰጠ! እስከ ህቅታ ታምኖ የኖረው አርበኛ ሽህ ጨለፎችን አሰልጥኖ መሪ አድርጎ ታጋዮች አድርጎ አንድያ ህይዎቱን ለአማራ ህዝብ ህልውና ሰጠ!
የተሰዋህለትንና ውድ ህይወትህን የከፈልክለትን አላማ ከግብ እናደርሳለን!
አፋብን ወሎ ቤተ-አማራ ምኒልክ ዕዝ
ሚያዚያ 22/2018 ዓ.ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top