የራስ አበበ አረጋይ ክፍለ ጦር የማያዳግም እርምጃ ወሰደ።

ለጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ የሚሆን ህትመቶችን በማዘጋጀት ላይ በሚገኙ የብልፅግና የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ አባትን ባጀቡ የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻና ፖሊሶች ላይ ምህታተኛው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለ ጦር የማያዳግም እርምጃ ወሰደ።
ግንቦት 16/2018 ዓ.ም።
የአገዛዙን ዕድሜ ለማራዘም ቀን ከለሊት በሚታትሩ ሆድ አደሮች ላይ ድርጅታችን አፋብን ባስተላለፈው የማስጠንቀቂያ መልዕክት መሰረት የሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ አፄ አምደ ፅዮን ኮር ጀግናው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር አገዛዙ ወደ ኦሮሚያ ባካለለው በግራርያ (ፍቸ ሰላሌ) አውራጃ ደብረ ፅጌ ወረዳ ድረስ ዘልቀው በመግባት በትላንትናው ዕለት ከምሽቱ 3:30 ላይ በብልፅግናው አገልጋዮች ላይ የማያዳግም ርምጃ ሲወስድ የምርጫ ቁሳቁሶችንና የህትመት መሳሪያዎችን እንዲሁም 3 ክላሽኮቭ መሳሪያ፣ አንድ ምርኮኛ የኦሮሚያ ሚሊሻ እና የግፍ እስረኞችን በተኩስ ልውውጥ በማስለቀቅ ግዳጁን በሚገባ በመፈፀም ወደመጣበት ቀጠና ተመልሷል ሲል የአፄ አምደ ፅዮን ኮር ገለፀ።
አገዛዙ ህዝባችንን ለተጨማሪ 5 የመከራ ዓመታት ለመዳረግ ለጎዳና ላይ የምርጫ ቅስቀሳ የሚሆን ህትመቶችን በማዘጋጀት ላይ በሚገኙ የብልፅግና የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ አባትን ባጀቡ የአገዛዙ ወንበር አስጠባቂ ሚሊሻና ፖሊሶች ላይ ምህታተኛው የአፄ አምደ ፅዮን ኮር አሃድ የሆነው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለጦር የማያዳግም ርምጃ መውሰዱን ኮሩ በግንባር መረጃው ገልጿል።
ይህ በእንዲሕ እንዳለ በደነባ ከተማ የመሸጉት የሰርዓቱ አገልጋይ ሆድ አደሮች መካከል በተፈጠረ ያለመግባባት በተደረገ የተኩስ ልውውጥ በትላንትናው ዕለት ከምሽቱ 3:00 ጀምሮ እርስበርሳቸው መጨፋጨፋቸውን የአፄ አምደ ፅዮን ኮር መረጃና መገናኛ ክፍል አስታወቀ።
በሸዋ ክፍለ ሀገር በሲያደብርና ዋዩ ወረዳ ደነባ ከተማ ውስጥ መሸጎ የሚገኘው የፋሽስቱ ዓብይ ዓህመድ ወንበር አሰጠባቂ እረሱን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ብሎ በሚጠራውና የኦሮሙማው ምንጣፍ ጎታች ሚኒሻ ጎራ ለይቶ ሲታኮሰ ያመሸ ሲሆን የደነባ ከተማ ሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ የሆነው አቶ የኋሉ በልሁ ከነ አጃቢዎቹ በመከላከያ ሲገደል ፣ ሁለት የመከላከያ አመራሮችና 4አባላትን ጨምሮ፣ 2 የከተማ ፖሊስ እና 3 የሚኒሻ አባላት የተገደሉ ሲሆን፣ 7 የሚሊሻ አባላት፣ 3 መከላከያ በሞት አፋፍ ላይ ሆነው በደነባና ደብረ ብርሃን ሆስፒታል ይገኛሉ ሲል ኮሩ በመረጃው ገልጿል።
አጅግ አስገራሚው ነገር የግጭቱ መንሰኤ በሆቴል ውስጥ እያሉ በከፍተኛ የአልኮል መጠጥ ላይ በነበሩበት ወቅት “ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል” እንደተባለው ምርጫን በተመለከተ ሲከራከሩ በመከላከያ ሰራዊት አመራሩ በኩል “ህዝብ የፈለገውን ይምረጥ አታሰገድዱት” የሚል የመከራከሪያ ሀሳብ በማምጣቱ ከወረዳው የሚሊሻ ጽ/ቤት ኃላፊ ጋር ግጭት ውስጥ በመግባት የተጀመረ ሲሆን በተፈጠረው አለመግባባት ሁለቱም መሞታቸውን ኮሩ አረጋግጧል።
በወረዳው አዲሰ አለም ቀበሌ ዜጎች የሚሰቃዩበትን ፖሊሰ ጣቢያ በጀግናው የራስ አበበ አረጋይ ክፍለ ጦር
ቃኝወች የተሰበረ ሲሆን ለሰርዓቱ ወንበር ማሰጠበቂያ እና ዜጎች የሚሰቃዩበት ሰነዶችና፣ የፓርቲ የገንዘብ መዋጮ ደረሰኞችን፣ የህትመት መሳሪያ በቁጥጥር ስር ያዋሉ ሲሆን በተጨማሪ የፖሊሰ ጣቢያው ዘበኞች ሲጠቀሙበት የነበረው የጦር መሳሪያም ጭምር በቁጥጥር አውሏል።
”ክብር ለትግሉ ሰማዕታት”
ህልውናችን በተባበረ ክንዳችን
የአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት አሳምነው ዕዝ
ግንቦት 16/2018 ዓ.ም

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top